"የኛ ለሁሉም"
የቁጠባ አገልግሎት
የገንዘብ ስርዓታችንን ለማሻሻል፣ የራሳችንን ቸግር በራሳችን ለመፍታት፣ ለምንፈልገው ጉዳይ ማዋል የምንችለውን ገንዘብ እንዲኖረን፣ በጋራ ሆነ በግል ለምንሰራው ስራ የመነሻ ካፒታል ሆኖ የሚያገለግለንና ያለንን የመወሰን አቅም የሚያዳብርልን ባለሀብት መሆን ስለምንጀምር በማህበረሰባችን ውስጥ ያለን ስፍራና ተሰሚነት ከፍ ያደርጋል፡፡
የውዴታ ቁጠባ
“የኛ ለሁሉም”
ይህ የቁጠባ ዓይነት ግለሰቦች በውዴታ የሚያስቀምጡት ሲሆን የኛ ማይክሮ ፋይናንስ በዚህ ቁጠባ ላይ ጠቀም ያለ ወለድ ይከፍላል፡፡ የውዴታ ቁጠባ ላይ ኩባንያችን ማራኪ የቁጠባ ወለድ ይከፍላል፡፡
የታዳጊ ልጆች ቁጠባ
“የኛ ለሁሉም!”
ከ 15 ዓመት በታች ለሆኑ ታዳጊ ልጆች የተዘጋጀ የቁጠባ ዓይነት ነው፡፡ በዚህ ቁጠባ ላይ የኛ ማይክሮ ፋይናንስ ማራኪ ወለድ ይከፍላል፡፡
የሳጥን ቁጠባ
“የኛ ለሁሉም”
ከ 15 ዓመት በታች ለሆኑ ታዳጊ ልጆች የተዘጋጀ የቁጠባ ዓይነት ነው፡፡ በዚህ ቁጠባ ላይ የኛ ማይክሮ ፋይናንስ 9 በመቶ ወለድ ይከፍላል፡፡
የጊዜ ገደብ ቁጠባ
“የኛ ለሁሉም!”
በዋነኝነት ለተለያዩ ተቋማትና ድርጅቶች የተዘጋጀው ይህ የቁጠባ ዓይነት ማራኪና ጠቀም ያለ ወለድ የሚያስገኝ ነው፡፡ በጊዜ ገደብ በውል የሚቀመጠው ይህ የቁጠባ ዓይነት እንደተቆጠበው የገንዘብ መጠንና እንደሚቆይበት ጊዜ እጅግ ማራኪ የሆነ ወለድ ያስገኛል፡፡
የተቋማት ቁጠባ
“የኛ ለሁሉም”
ይህ የቁጠባ ዓይነት በዋነኝነት የተዘጋጀው ለእድሮች ፣ ለእቁብ ማህበራት እና ለተለያዩ ሌሎች ማህበራት ነው፡፡ ለተቋማት ቁጠባ ዝቅተኛው የወለድ መጠን ማራኪ ነው፡፡
የሴቶች ቁጠባ
“የኛ ለሁሉም!”
ይህ የቁጠባ አይነት በአ.ማህበሩ ቁጠባ ለመቆጠብ ፍላጎት ያላቸው ሴቶች ለማበረታት የተጀመረ የቁጠባ አይነት ነው፡፡ አ.ማህበሩ ወሩን ሙሉ ለተቀመጠ ተቀማቸጭ 9% (ዘጠኝ በመቶ) ወለድ ይከፍላል፡፡ ገንዘቡን የድርጅቱ ደረሰኝ ሳይቆረጥ መቀበል በጥብቅ የተከለከለ ነው፡፡