"የኛ ለሁሉም!"

የብድር አገልግሎት

SME loan

የአነስተኛ እና መካካለኛ ኢንተርፕራዝ ብድር

“የኛ ለሁሉም!”

ይህ የብድር ዓይነት በዋነኝነት የታሰበው ለአነስተኛ እና መካከለኛ ኢንተርፕራዞች ሲሆን በጅምር ደረጃ ላሉት ወይንም ቀድሞውንም በከተማና በገጠር በንግድ ሥራ ላይ ለተሰማሩት ነው፡፡ ብድሩ ለስራ ማስኬጃ ካፒታል ፣ ለቋሚ ንብረት ግዥ እንዲሁም ንግዱን ለማቀላጠፍና ለመደገፍ ይውላል፡፡

የየኛ ማይክሮ ፋይናንስ አ. ማ. የአነስተኛና መካከለኛ ኢንተርፕራዞች ብድር የብድር መጠን ለግለሰብ ተበዳሪዎች የካፒታላችን አንድ ፐርሰንት ሲሆን ለድርጅት ተበዳሪዎች ደግሞ የካፒታላችን አራት ፐርሰንት ይሆናል፡፡ የብድር መጠኑ የሚወሰነው በንግድ ሥራው ትርፋማነት ፣ በንግዱ ዘላቂነት እና በተቆጠበ የገንዘብ መጠን ላይ በመመርኮዝ ነው፡፡

የጥቃቅን ንግድ ብድር (የግለሰብ)

“የኛ ለሁሉም!”

የጥቃቅን ንግድ ብድር አዲስ ሥራ ለመጀመር ወይም ያለውን የንግድ ሥራ ለማስፋት ሊውል ይችላል፡፡ ይህ የብድር ዓይነት በተለይም የጥቃቅን ኢንተርፕራዞችን ፣ የሴቶችንና የወጣቶችን ፍላጎት መሠረት ያደረገ ብድር ሲሆን ማህበራዊ ኃላፊነትን የመወጣት ዓላማ ይኖረዋል፡፡ በጥቃቅን ንግድ ብድር የሚጠቀሙት ነጋዴዎች በተለይም በከተማና በገጠር በጥቃቅንና አነስተኛ ንግድ ሥራ ላይ የተሰማሩ ሴቶች ናቸው፡፡

የየኛ ማይክሮ ፋይናንስ የጥቃቅን ብድር መጠን ለአንድ ግለሰብ የካፒታላችን አንድ ፐርሰንት ነው፡፡ ሆኖም የብድሩ መጠን የሚወሰነው በተበዳሪው በተቀመጠው የንግድ ዕቅድ ትርፋማነት ላይ በመመስረት ነው፡፡

micro loan
cosumption loan

የፍጆታ ብድር (የሠራተኛና ተቀጣሪ ያልሆነ)

“የኛ ለሁሉም!”

የሠራተኞች የፍጆታ ብድር ለማንኛውም የግል ዓላማ እንደ ህክምና ወጪ ሽፋን ፣ የትምህርት ክፍያ ፣የቤት ዕቃዎች ግዥ እና ሌሎች የግል ወጪዎችን ለመሸፈን ይውላል፡፡ ይህ የብድር ዓይነት ከአምራችና ከንግድ ሥራዎች ውጪ የተለያዩ ግላዊና ማህበራዊ ግዴታዎችን ለማሟላት የሚሰጥ ነው፡፡

የሠራተኞች የፍጆታ ብድር ከፍተኛው የብድር መጠን ለአንድ ተበዳሪ እስከ ብር 80000.00 ነው፡፡

የግብርና ብድር

“የኛ ለሁሉም!”

የግብርና ብድር መካከለኛ ገቢ ላለው አርሶ አደር ተበዳሪ የግብአት ግዥ ፣ የማዳበሪያ ግዥ ፣ የተሻሻለ ዘር ግዥ ፣ የመሬት ኪራይ ክፍያ ፣ የእርሻ ግብዓቶእ ግዥ እንዲሁም ሌሎች የግብርናና የማድለብ ሥራዎችን ለማከናወን ሊውል ይችላል፡፡

agricalture loan
loans_593001320

የቋሚ ንብረት ግዥ ብድር

“የኛ ለሁሉም!”

የቋሚ ንብረት ግዥ ብድር መካከለኛ ገቢ ላላቸው ተበዳሪዎች የተሸከርካሪ ፣ የቴሌቪዥን ፣ የሞተር ሳይክል ፣ ፍሪጅ ፣ ጀነሬተር ፣ የቤት ዕቃዎች ፣ የእርሻ ማሽነሪዎች ፣ የባዮ ጋዝ ዕቃዎች ፣ የውሃ ፓምፖች ፣ የሞባይል ስልክ እና መለዋወጫዎች እንዲሁም ሌሎች ቋሚ ንብረቶችን ለመግዛት የሚውል ይሆናል፡፡

የቋሚ ንብረት ግዥ ብድር ከፍተኛው የብድር መጠን ለግለሰብ ብድር የኩባንያው ካፒታል አንድ መቶኛ ነው፡፡

የመኖሪያ ቤት ብድር (የግንባታ ብድር)

“የኛ ለሁሉም!”

የመኖሪያ ቤት ወይም የግንባታ ብድር ከሌሎቹ የብድር ዓይነቶች ጋር ሲነጻጸር በረዥም ጊዜ የሚከፈል የብድር ዓይነት ሲሆን በግንባታ ላይ ያለን ህንጻ ለመጨረስ ፣ ለጋራ መኖሪያ ቤቶች ክፍያ ለመሸፈን ፣ የአነስተኛ የንግድ ሱቅ ግንባታ እና ተጨማሪ ክፍሎችን ለመገንባት የሚውል ይሆናል፡፡

የመኖሪያ ቤት ወይም የግንባታ ብድር ከፍተኛው የብድር መጠን የኩባንያው ካፒታል አንድ ፐርሰንት ነው፡፡

construction loan