ወደ የኛ ማይክሮ ፋይናንስ አ. ማ. እንኳን ደህና መጡ!

"ልናገለግልዎ ቆርጠን ተነስተናል!"

የኛ ማይክሮ ፋይናንስ አ.ማ በፋይናንስ አገልግሎት ዘርፍ የላቀ እና ጥራት ያለው አገልግሎት ለመስጠት በአገሪቱ የኢኮኖሚ ዕድገት የበኩሉን አስተዋፅኦ ለማበርከት የተቋቋመ ነው፡፡ በውጤቱም ሀብት በመፍጠርና ትርፍ የሚያስገኙ የንግድ እንቅስቃሴዎችን የገንዘብ እገዛ በማድረግ ሞያዊ እና ማህበራዊ አገልግሎቶችን በመስጠት ላይ እንገኛለን፡፡ በቡድን በመስራት እናምናለን ፤ እንዲሁም ከደንበኞቻችን ጋር አብረን በመስራት ግባችን ላይ እንደርሳለን፡፡

አገልግሎቶቻችን

"የኛ ለሁሉም!"

የቁጠባ አገልግሎት

የገንዘብ ስርዓታችንን ለማሻሻል፣ የራሳችንን ቸግር በራሳችን ለመፍታት፣ ለምንፈልገው ጉዳይ ማዋል የምንችለውን ገንዘብ እንዲኖረን፣ በጋራ ሆነ በግል ለምንሰራው ስራ የመነሻ ካፒታል ሆኖ የሚያገለግለንና ያለንን የመወሰን አቅም የሚያዳብርልን ባለሀብት መሆን ስለምንጀምር በማህበረሰባችን ውስጥ ያለን ስፍራና ተሰሚነት ከፍ ያደርጋል፡፡

"የኛ ለሁሉም!"

የብድር አገልግሎት

የአነስተኛና መካከለኛ ኢንተርፕራይዞች ብድር፣ የጥቃቅን ንግድ ብድር ፣ የፍጆታ ብድር ፣ የየግብርና ብድር፣ የቋሚ ንብረት ግዥ ብድር ፣ የመኖሪያ ቤት ብድር፣ ልዩ ብድር እና ሌሎችንም የብድር አገልግሎቶች እናቀርባለን።

"የኛ ለሁሉም!"

የስልጠናና የማማከር አገልግሎት

የኩባንያው ሠራተኞች የብቃት ሚስጥር በየወቅቱ የሚሰጣቸው ሞያዊ ስልጠና ነው፡፡ የኛ ማይክሮ ፋይናንስ አ. ማ. ለክቡራን ደንበኞቹ ከብድርና ቁጠባ በተጨማሪ ለንግድ ሥራቸው የሚጠቅም የስልጠናና የማማከር አገልግሎት ለመስጠት አስፈላጊውን ዝግጅት አጠናቋል፡፡

"የኛ ለሁሉም!"

ስለ እኛ

"የኛ ለሁሉም!"

የኛ ማይክሮ ፋይናንስ አ.ማ የተመሰረተው የላቀ የሞያ እና ከፍተኛ ጥራት ያለው የፋይናንስ አገልግሎት ለሚፈልጉ ግለሰቦችና በአነስተኛና መካከለኛ ኢንተርፕራየዝ ለታቀፉ ህጋዊ ማህበሮች በመስጠት ለሀገር ኢኮኖሚ ዕድገት የበኩሉን አስተዋጽኦ በማበርከት ሀብት ለመፍጠርና ትርፍ ለማግኘት ነው፡፡

የእኛ መርሆዎች እና እሴቶቻችን

“የኛ ለሁሉም!”

የኛ - ልዩነታችን

"የኛ ለሁሉም!"

አጋሮቻችን

"የኛ ለሁሉም!"

ደንበኞቻችን

የኛ ማይክሮ ፋይናንስ አ.ማ ትኩረት የሚያደርግባቸው ደንበኞች ፤ ከባንኮች አገልግሎት ማግኘት ያልቻሉትን ፣ መስራት የሚችሉ በተለይም በጥቃቅን ፣ አነስተኛና መካከለኛ ንግድ ሥራ ላይ የተሰማሩ ወጣቶች እና ሴቶች ላይ ነው፡፡ በዋነኝነት በአዲስ አበባ እንዲሁም በመላው ሀገሪቱ የሚገኙትን  ደንበኞች እናገለግላለን፡፡